ሰርግ በተክሊል
የጋብቻ ሥርዐት ቃል ኪዳን፦ ዐቅመ ሔዋንን የደረሰች ድንግል ልጅ አገረድና (ቆንጆ) ዐቅመ አዳምን ያደረሰ ድንግል ወንድ በተክሊል ሥርዐት ተጋብተው ባልና ሚስት ለመኾን ከቄሱ እጅ የቃል ኪዳን ቀለበትን ተቀባብለው የጋብቻ ሕግን የሚያጸኑበትና አንድ አካል አንድ አምሳል ለመኾን የቤተ ክርስቲያን ሥርዐት የተክሊል ጋብቻ መጽሐፈ ተክሊል ነው ወይም ፈቶች ያልኾኑ ድንግል ሴትና ድንግል ወንድ ሲጋቡ ማለት ነው።
የክርስቲያን ጋብቻ ሥነ ሥርዐት ሙሽራውና ሙሽራዬቱ አክሊል ተቀዳጅተው አበባ ይዘው አንድ መጐናጸፊያ ለብሰው የተባረከ ቀለበት አድርገው ቃላ ኪዳን የሚገቡበት ሥጋውንና ደሙን የሚቀበሉበት መንፈሳዊ ሕግ እስከ ሞት ድረስ አለመፋታትንና አለመለያየትን የሚሰብክ የሚያስተምር ለሥጋም ለነፍስም ጥቅም የሚኾን ነው።
Comments
Post a Comment